እውነት የኢትዮጵያ እምፓየር የመከላከያ ኃይል የሰላም አርበኛ ነው?

Published Jan. 1, 2024, 5:51 p.m. by Birhaanuu Hundee

681




- ከArts Tv World ጋር የተደረገው የጀዋር መሃመድ አነጋጋሪ ቃለ መጠየቅ -
በብርሃኑ ሁንዴ
Arts Tv World በሚባል ሚድያ ላይ በአቶ ደረጀ ኃይሌ ከኦቦ ጀዋር መሃመድ ጋር የተደረገውን ቃለ መጠየቅ ክፍል አንድ
አዳምጬ አንዳንድ ነገሮችን ታዘብኩኝ። ወደ ጉዳዩ ከመግባቴ በፊት እስቲ ኦቦ ጀዋር ያላቸውን አንዳንድ ጥቂት ነገሮችን
ልጥቀስ፥
“የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመበላሸቱ የተነሳ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ ቀረና አብዛኛው የፖለቲካ ስራ በመከላከያ ላይ
ወድቋል።
የኛ መከላከያ ዛሬ የአገር ውስጥ ጦርነትን ጠልቷል። ጀኔራሎቻችን መዋጋት በቃን እያሉ ነው።
ዛሬ ላይ ጦርነት የሚፈልግ ኢትዮጵያ ውስጥ ሲቪልም የለም፤ ባለ መለዮም የለም፤ ሚንስቴርም የለም። በጣም
እየቀነሰ መጥቷል።
ዛሬ No 1 የሰላም አርበኛ ወታደር ነው። ከወንድሞቹ ጋር መገዳደል ሰልችቶታል። አነጋግሬአቸዋለሁ።”
እኔ ግን የማይገባኝና ጥያቄ የሆነብኝ ነገር ጀዋር መሃመድ የመንግስት ተቃዋሚ ነው ወይንስ የመንግስትን ሀሳብ የሚደግፍና
አማካሪም ነገር ነው? ይህንን ጥያቄ ማንሳት የቻልኩበት ምክንያት ከዚህ በፊት “Haala Keessa Jirruu fi
Boqonnaa Qabsoo Itti Aanu” በሚል ርዕስ በአፋን ኦሮሞ (Afaan Oromoo) ባቀረበው ሰፊ ፅሁፍ ውስጥ
ባብዛኛው የብልፅግናን መንግስት የሚመክርና የነሱ አገዛዝ ተሻሽሎ እንዲቀጥል ሲገልፅ እንደነበር የሚታወስ ነው። አብይ
አህመድ ገና ወደ ስልጣን ሲመጣ ጀዋር ሲቃወም እንደነበረ ይታወሳል። ነገር ግን ጀዋር እላይ የተጠቀሰውን ፅሁፍ ከማቅረቡ
በፊት አብይንና አገዛዙን ከውድቅት ለማዳን ጥረት ሲያደርግ እንደነበር የማይካድ ነው። ሹፌሩ አብይ አህመድ የሆነና ወደ ገድል
ልገባ አፋፍ ላይ ያለውን አውቶቡስ በጀዋር ሲጎተተ እንደ ምስል ታይቶ የነበረው ጉዳይ ያለ ምክንያት አልነበረም።
ወደ ፅሁፌ ርዕስ ልመለስና፣ ማንም ሰው የሚያውቀውና ከዓለም ማህበረሰብ ያልተደበቀ እውነታ የኢትዮጵያ የመከላከያ
ሰራዊት አባላት ሰላማዊ ሰዎችን ከቤታቸው በማውጣት የምገድሉ፤ ሴቶችን የምደፍሩና የምያሰቃዩ፤ ሽማግሌዎችን በአደባባይ
የምያንገላቱና የምያዋርዱ፤ ሰዎችን ከእስር ቤት አውጥተው የምረሽኑ፤ ልጅሽ እኛን ልወጋ ጫካ ነው ያለው ብለው እናትን
ከቤት አውጥተው የምያንገላቱና በመጨረሻም ረሽነው ሜዳ ላይ የምጥሉ፤ የሰላማዊ ገበሬዎችን ቤት በእሳት እያጋዩና ቤቱ
ሲቀጣጠል በአጠገቡ ፎቶ የምነሱ፤ የሕዝብን ንብረት የምዘርፉና መዝረፍ ያልቻሉትን የምያወደሙ ኃይሎች እውነት እስቲ
የሰላም አርበኛ ይባላሉ? ይህ እውነታ ከኦቦ ጀዋር ተደብቆ ይሆን? ይህንን ሁሉ ሳያውቅ ቀርቶስ ይሆን? እየተሰቃየ ያለው
የኦሮሞ ሕዝብ እሱ ከእብራኩ የወጣ አይደለም? የዚህ ሕዝብ ስቃይ አይታየውም? እንዴት የሕዝብን ገዳይ የሰላም አርበኛ
ይላል? ወታደሮቹ ከወንድሞቹ ጋር መገዳደል ሰልችቶታል። አነጋግሬአቸዋለሁ። ይላል። ነገር ግን ይህ በመሬት ላይ ያለ እውነታ
ነው?
ሌላው የሚገርመው ነገር “የኛ መከላከያ ዛሬ የአገር ውስጥ ጦርነትን ጠልቷል። ጀኔራሎቻችን መዋጋት በቃን እያሉ ነው።”
ማለቱ ከኦሮሞ ሕዝብ ይልቅ ምን ያህል ለእምፓየሯ ጠባቂዎች እንደሚወግን ያሳያል። “ዛሬ ላይ ጦርነት የሚፈልግ ኢትዮጵያ
ውስጥ ሲቪልም የለም፤ ባለ መለዮም የለም፤ ሚንስቴርም የለም። በጣም እየቀነሰ መጥቷል።” ማለቱ ደግሞ ፍፁም
ከእውነታ የራቀና መሬት ላይ ያለውን ጉዳይ የሚፃረር ነው። የእምፓየሯ የጦር ኃይሎች ዕታማጆር ሹም ራሱ ስናገር በድሮን
እንዋጋለን፤ የገዛናቸውም ለማሳየት ሳይሆን እንደ ማንኛውም የጦር መሳሪያ ልንዋጋበት ነው ወዘተ እያለ መፎከሩ ሕዝብን
በድሮን ለመጨፍጨፍ በመሆኑ ይህ የሚያሳየው ለሰላም ሳይሆን ለጦርነት እንደተዘጋጁ ነው። ታዲይ ይህ በአደባባይ እየታየ ኦቦ
ጀዋር እንዴት የሰላም አርበኛ ብሎ ይጠራቸዋል? ሌላው “የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመበላሸቱ የተነሳ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ
ቀረና አብዛኛው የፖለቲካ ስራ በመከላከያ ላይ ወድቋል።” ያለው እውነት ነው። የእምፓየሯ ፖለቲካ መበላሸቱን ማመኑ ጥሩ
ነው። አገሪቷንም እያስተዳደረ ያለው ጠመንጃና የማፊያ ቡድን እንጂ ፖለቲካዊ የአስተዳደር መዋቅር እንደሌለ ጀዋርም አምኗል
ማለት ነው።
ሌላው ኦቦ ጀር የPPን መንግስት ማሞጋሱ የሚታወቀው በትግራይ ጦርነት ላይ መንግስት ወይም አሱ በይበልጥ
የሚያሞግሰው የመከላከያ ሰራዊት መቀሌን በኃይል መያዝ ስችሉ ግን ከአብይ መንግስት ሰላም ፈላጊነት የተነሳ የፕሪቶሪያው
ስምምነት እንዲደረግ ተወሰነ ማለቱ የሚገርም ነው። በጀዋር አቀራረብ ድምዳሜው የሚያመላክተው መንግስት ሁሉንም
በኃይል ማሽነፍ እየቻለ ግን ሰላም ፈላጊ እንደሆነ ነው። ይህ ማለት የኦሮሞ የነፃነት ሰራዊት (WBO)ም በታንዛኒያ ለምክክር
መቀመጡ በመንግስት መደምሰስ ስችል ግን በመንግስት ርህራሄነትና ሰላም ፈላጊነት በመሆኑ ነው ማለት ነው።
ትደመሰሳላችሁና እጅ ስጡ፤ መሳሪያ አስረክቡ የምለውን የPPን ከንቱ ዛቻ መጋራቱ ነው። ይህ እኮ አይደንቅም!! ጀዋር
መቸ WBOን ደግፎ ያቃል፧ በሰላማዊ የትግል ስም ሁሌም የWBOን የትጥቅ ትግል ይቃወማል። ለዛሬው ያለኝን አስተያየት
በዚሁ ልቋጭና ምናልባት ከክፍል ሁለት ቃለ መጠየቁ በኋላ በሰፊው እመለስበት ይሆናል? ብዙ የሚባሉ ነገሮችም ልኖሩ
ይችላሉ??


Similar posts:

Baqala Garba's Departure Could Be A Potential Catalyst for Armed Struggle: Analyzing his Exit in the Context of the OFC's Letter

የፓርቲ ፖለቲካ በኢትዮጵያ - ከፊውዳል አርስቶክራሲ እስከ አብዮታዊ ዲሞክራሲ

Harassment continued in Oromia| OLF-OLA Leaders Reveal Causes of Failure in Peace Deal

Paul Bernard Henze, a CIA Operative and Journalist's Advice to Meles to Destroy OLF